የተደበቀው የክርስቶስ አስተምህሮ - የቶማስ ወንጌል
ሰላም ለእናንተ ይሁን
ላለፉት ሁለት ሺህ አመታት ምድራችን ኢትዮጵያ በተቀደሰ ቃልኪዳን ኖራለች። ከላሊበላ ተራሮች እስከ ጣና ሀይቅ ጥንታውያን ገዳማት ድረስ የክርስቶስ ታሪክ በድንጋዮቻችን እና በነፍሳችን ላይ ተቀርጾ ይገኛል።
እኛ የመጽሐፉ ሰዎች ነን። በምድር ላይ ካሉት በጣም ጥንታዊ እና የተሟላ መጽሐፍ ቅዱሶች መሃል አንዱን እና ቀዳሚውን ይዘናል። የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት፣ ትውፊት እና ሥርዓተ ቅዳሴ በሕይወታችን ጠብቀን አኑረናል።
ነገር ግን በእነዚህ ውስጥ በጣም የሚያስፈልገን፣ በጣም ጥልቅ የሆነ የተደበቀ እውነት እንዳለ ብነግራችሁስ? አዲስ ትምህርት አይደለም። የውጭ ሀሳብም አይደለም። ነገር ግን የተደበቀ፣ ጥልቅ ትርጉም ያለው እና ለማንፀባረቅ በመጠባበቅ ላይ ያለ እንቁ ነው።
ኢየሱስ ያስተማረው ትልቁ ሚስጢር አንድ ቀን በሰማይ ስለሚመጣው የእግዚአብሔር መንግስት ብቻ ባይሆንስ?
…ነገር ግን በእያንዳንዳችን ውስጥ ስለሚኖረው መለኮታዊ ኃይል፣ የተቀደሰ መገኘት ቢሆንስ?
ክፍል 1፡ መንግስቱ ቦታ ሳይሆን መገኘት ነው
በክርስትና ሃይማኖት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እጅግ የተቀደሰው ነገር ታቦት ነው። የቃል ኪዳኑ ታቦት ምሳሌ ሲሆን መገኘቱ ሕንፃውን ቅዱስ ያደርገዋል። የእግዚአብሔርን በዛ በተቀደሰ ቦታ ውስጥ መኖርን ያሳያል። ይታያል፣ ይከበራል፣ ሀይሉም ይሰማል።
እንግዲህ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 17 ቁጥር 21 ላይ የሚገኘውን የኢየሱስን ቃል በጥሞና አድምጡ። ፈሪሳውያን የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ እንደምትመጣ በጠየቁ ጊዜ፥ እንዲህ ሲል መለሰላቸው።
"የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም፤ ደግሞም። እንኋት በዚህ ወይም። እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና" አላቸው።
እነዚህ ቃላት በልባችሁ አጢኑ። "የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና"
ይህ አባባል መልስ ብቻ ሳሆን መገለጥም ጭምር ነበር።
በታቦቱ ላይ ያለው ያው መገኘት፣ ያው መንፈስ ቅዱስ፣ በውስጣችን ማደርያውን እንዳደረገ እየነገረን ነበር።
እኛ የስጋ እና የአጥንት አካል ብቻ አይደለንም። እኛ ሕያው ቤተ መቅደስ ነን። የሚራመድ፣ የሚተነፍስ መቅደስ።
ይህ ለብዙቆቻችን በግላጭ የማይነገረን ትምህርት ነው። የሕንፃ ቤተክርስቲያን የጋራ ቅዱስ ስፍራ ቢሆንም እኛ በየግላችን የፈጣሪ ማደሪያዎች ነን።
ክፍል 2፡ አእምሮህ ('Hasab') እንደ የፍጥረት መሳሪያ
ጥንታዊ አባባሎቻችን ጥልቅ ጥበብን ተሸክመዋል። "ታጋሽ ሰው ድንጋይ ያበስላል" እንላለ። ይህ አባባል ጽናትን፣ ትኩረትን እና የእምነትን ሐይል ያሳያል።
ኢየሱስ ይህንን ያስተማረው በመንፈሳዊ ደረጃ ነው። ሀሳባችን በአእምሯችን ውስጥ የሚመላለሱ ጊዜያዊ ደመናዎች ብቻ አይደሉም። ዘሮች ናቸው። የተከልከውን ሀሳብ ሁሉ በትኩረት እናጠጣለን። እና በመጨረሻም ፣ በህይወታችን ውስጥ ፍሬ ያፈራል ።
በቅዱሱ መጽሐፍ ውስጥ "ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል።" ይላል።
ብዙዎቻችን ይህንን እናነብና ትኩረታችንን መጠየቅ ላይ እናተኩራለን። ምስጢሩ ግን መጠየቅ ሳይሆን እንደ ተቀበልን ማመን ነው።
እስቲ ስለችሚያስጨንቃችሁ ነገር አስቡ። አእምሮአችሁን በፍርሃት እና በጭንቀት ሲሞላ ለራሳችሁ ምን አይነይ አለም ነው የምትገነቡት?
ነገር ግን አዕምሮኣችሁ ውስጥ የተለየ ዘር ለመትከል ከሞከራችሁስ? የየፍቅር፣ የሰላም፣ የተስፋ እና የጸጋ ዘር ብትተክሉስ?
ይህ አስማት አይደለም. መለኮታዊ ህግ እንጂ። የአዕምሮኣችን እና የልብባችን ጉልበቶች ከአጽናፈ አለም የሚስቡት ሐይል ተመሳሳይ ነው። በውስጣችን ያለው አለም የውጪው አለም ነፀብራቅ ብቻ ሳይሆን ፈጣሪም ጭምር ነው።
ክፍል 3፡ ከበረሃ የተጋባ የኢትዮጵያውያን ሚስጥር
ይህ ወደ ውስጥ የመመልከት መንገድ ከምዕራቡ ዓለም የመጣ የአዲስ ዘመን ሃሳብ አይደለም። የራሳችን የአፍሪካ ክርስቲያናዊ ስልጣኔ ቅርስ አካል ነው። ለዘመናት ኢትዮጵያ የሊቃውንት፣ የበረሃ አባቶችና እናቶች መኖሪያ ሆና ቆይታለች።
ከተማዎችን እና መንደሮችን ትተው ወደ ተራሮች ጸጥታ ወደ በረሃው ብቸኝነት ይገባሉ። ለምን? ከዓለም እየሸሹ ነበር?
አይደለም፡ ወደ አንድ ነገር እየሮጡ እንጂ።
በዝምታ ወደ ሚኖረው አምላክ እየሮጡ ነበር። የእግዚአብሔርን ድምፅ በእውነት ለመስማት በመጀመሪያ የዓለምን ጩኸት እና የአዕምሮአቸውን ጫጫታ ጸጥ ማድረግ እንዳለባቸው ስለተረዱ ነው ሁሉንም ጥለው የሚመንኑት።
በብቸኝነት ሳሉ በጾም እና ማለቂያ በሌለው ጸሎት አንድ ነገር እየሠሩ ነበር፡ አንድነትን ለማግኘት ይጥሩ ነበር። አንድነት። ከመለኮት ጋር አንድ መሆን።
ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ብቻ አልነበረም። ፈጣሪን ራሱን ለመምሰል፣ በራሳቸው እና በፈጣሪ መካከል ያለውን ድንበር ለማጥፋት እና ኢየሱስ የተናገረውን መንግሥት እዚያው በልባቸው ጸጥታ ውስጥ ለማግኘት ፈልገው እንጂ።
ክፍል 4፡ የቶማስ ወንጌል - አከራካሪ ፍንጭ
በ1945 በናግ ሃማዲ ግብፅ — ከእኛ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጋር በጣም በተቆራኘች ምድር—አንድ አስደናቂ ግኝት ተገኘ።
ከእነዚህ ግኝቶች አንዱ የቶማስ ወንጌል ነው። የመጽሐፍ ቅዱሳችን ክፍል አይደለም። የተዋሕዶ ቀኖና የተቀደሰ እና የተሟላ ነው። ነገር ግን እነዚህን ጥንታዊ ድምጾች ማዳመጥ አንዳንድ ጊዜ የያዝናቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት በአዲስ ብርሃን እንድንረዳ ይረዳናል።
የቶማስ ወንጌል የኢየሱስ አባባሎች ስብስብ ነው። በውስጡም የራሳችንን የበረሃ ሚስጥሮች የሚመስለውን ሀይለኛ መግለጫዎችን እናገኛለን፡-
"ኢየሱስም አለ፡- በውስጣችሁ ያለውን ካወጣችሁት የምታወጡት ያድናችኋል፣ ባውስጣችሁ ያለውን ካላወጣችሁት ያላወጣችሁት ያጠፋችኋል።"
በደንብ አስተቅለን የምናስብ ከሆነ መዳናችን ከውጭ ብቻ የተሰጠ እንዳልሆነ እንረዳለን። በቅስጣችን የተቀበረ አቅም አለ። የእኛ ተግባር ወደ ውጪ ማውጣት ነው።
"ይህንን አለማድረግ፣ በውስጣችሁ ያለውን ሀብት ችላ በማለት ሙሉ ህይወታችሁን መምራት ነው"... ይላል ጽሑፉ። ይህም ወደ ጥፋት ይወስዳል፣ በፈጣሪ ቅጣት ሳይሆን ከራሳችን መለኮታዊ ምንጭ በመለያየታችን ብቻ።
ይህ የማንቃት ጥሪ ነው። ንቃ! ተነስ! መዳንህ በአንተ እና በእግዚአብሔር መካከል ነው ያለው፣ እና ድርሻህ በውስጥህ ያለውን መለኮትነት ማውጣት ብቻ ነው።
ክፍል 5፡ መንግሥቱን በዕለታዊ የኢትዮጵያ ሕይወታችን ማግኘት
ታዲያ እንዴት ነው "ውስጣችን ያለውን ሐይል የምናወጣው? እኛም ወደ በረሃ መሄድ አለብን?
የለብንም. የፈጣሪን መንግሥት በራሳችን ባህል እና ትውፊት ውስጥ ማግኘት እንችላለን።
የቡና ስነ ስርአታችንን አስቡ። ቡና መጠጣት ብቻ ይመስላችሁአል?
ቡና በፍቅር እና በተከፈተ ልብ ሆናችሁ ስታካፍሉት፣ እዚያው ቤታችሁ ውስጥ የመንግሥተ ሰማያትን ትንሽ ቀዳዳ ታገኛላችሁ። ይኸውም ሰላም ነው።
ደቦን አስቡ፣ መንደሩ ሁሉ አንድ ላይ ተሰባስቦ ለተቸገረ ቤተሰብ እርሻ ሲያርስ። በተግባር የሚታይ ፍቅር ማለት ነው። በውጫዊው ዓለም የሚታይ የውስጣዊ አንድነታችን ማረጋገጫ ይህ ነው።
መስቀሎቻችን ላይ ያሉትን አብነቶች ተመልከቱ።በጣም ውስብስብ ናቸው, ለዘላለም የሚቀጥሉ ይመስላሉ። ብቻቸውን የመንፈስ መረጋጋት የሚሰጡ፣ ማለቂያ የሌላቸው፣ ውስብስብ እና ውብ የእግዚአብሔር ተፈጥሮ ምልክት ናቸው።
ይህ መለኮታዊ ኃይል ረቂቅ ሀሳብ አይደለም። ቡና ላይ ያለው የአንድነት ስሜት ነው። በደ ውስጥ ያለው የልግስና መንፈስ ነው። በልብሳችን የተሸመነ ፍቅር እና በጸሎታችን ውስጥ የሚገኘው ሰላም ነው።
ከእግዚአብሔር ጋር መኖር ማመን ብቻ አይደለም። ቡናውን እንዴት እንደምትቀዱ፣ ጎረቤታችሁን እንዴት ሰላም እንደምትሉ፣ ስራችሁን እንዴት እንደምትሰሩ ነው። በምትሠሩት እያንዳንዱ ትንሽ ነገር ላይ የፍቅር እና የመገኘት መንፈስ ማምጣት ነው።
የመጨረሻ መልእክት
የእግዚአብሔር መንግሥት ከሞትክ በኋላ የምትሄድበት መድረሻ አይደለም። አሁንያለህበት የማንነትህ እውነታ ነው።
"የእግዚእብሔር መንግስት በውስጣችሁ ናትና"
ቅዱሱ ታቦት በቤተክርስቲያን ውስጥ ይገኛል ይህም የእግዚአብሔር መገኘት ምሳሌ ነው።
አንተ ግን ሕያው ታቦት ነህ የእግዚአብሔር ህልውና በአንተ ውስጥ ነው።
የሌለህን ሃይል ከውጭ አትፈልግ። ወደ ውስጥ ተመልከት እና የነበረውን ኃይል አውጣ።
ይህ አዲስ ሃይማኖት አይደለም። ይህ የጥንታዊው ተዋሕዶ እምነታችን ጥልቅ ገጽታ ነው። ስለ እግዚአብሔር ከማወቅ እግዚአብሔርን ወደማወቅ የሚደረግ ጉዞ ነው።
መቼም አቅመ ቢስ አልነበርክም።
ሁሌም መለኮታዊ ነበርክ።
ስለዚህ ጥያቄው "እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው ወይስ አይደለም?" ሳይሆን...
"በአንተ ውስጥ ካለው አምላክ ጋር ለመሆን ዝግጁ ነህ?"
ይህ መልእክት መንፈሳችሁን ከነካው ለወዳጃችሁ አካፍሉት። በሚቀጥለው የቡና ሥነ ሥርዓታችሁ ላይም ለቤተሰብዎ ያካፍሉ። ከጓደኞቻችሁም ጋር ተወያዩ።
ስጋዊ አካል
አካል የነፍስ ተላላኪ ነው፤ ውስጥ ያለውን ጨለማ/ብርሃን በስጋ ይገልጣል!
ነፍስ
ነፍስ ብቻዋን በዋጠችው እሳት ትቃጠላለች! (ነፍስ ወንድ ነው ሴት 🤔)
መንፈስ
መንፈስ የማይሰማ ግን በህይወት የሚስተጋባ ድምፅ ነው!
ስጋዊ አካል
አካል የነፍስ ተላላኪ ነው፤ ውስጥ ያለውን ጨለማ/ብርሃን በስጋ ይገልጣል!
ነፍስ
ነፍስ ብቻዋን በዋጠችው እሳት ትቃጠላለች! (ነፍስ ወንድ ነው ሴት 🤔)
መንፈስ
መንፈስ የማይሰማ ግን በህይወት የሚስተጋባ ድምፅ ነው!